የአዲስ እድርና መረዳጃ ማኀበር መተዳደሪያ ደንብ
የአዲስ እድርና መረዳጃ ማኀበር መተዳደሪያ ደንብ
ምዕራፍ 1 ጠቅላላ ድንጋጌ አንቀጽ 1.1 ስያሜ
1፡1፡1 ይህ ማኀበር አዲስ አድርና መረዳጃ ማኀበር ተብሎ ይጠራል።
አንቀጽ 1፡2 አድራሻና አቋም
1፡2፡1 የእድሩ አድራሻ በጆርጂያ አትላንታ ከተማ ነው።
1፡2፡2 እድሩ ጆርጂያ ሕግ መሰረት የተቋቋመና ለትርፍ የማይሰራ ድርጅት ነው።
1፡2፡3 እድሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው።
አንቀጽ 1፡3 ዓላማ
1፡3፡1 የእድር አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ሲለይ ለቀብር ስነ – ስርዓት ማስፈጸሚያ ወይም ለአስከሬን መላኪያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ፣
1፡3፡2 አባል ወይም የአባል ቤተሰብ ሲሞት የእድሩ አባላት ለቅሶ እንዲደርሱና እንዲያስተዛዝኑ፣ መረጃ ማዳረስና ማስተባበር፣
1፡3፡3 የለቅሶ ሥራን ማከፋፈል፣
1፡3፡4 አባላት የሟችን ቤተሰብ እንዲአጽናኑና በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ እዲተባበሩ ማድረግ፣
1፡3፡5 ለቀብር አፈጻጸም ወይም ለአስከሬን ማጓጓዝ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ለሟች ቤተሰብ መስጠት፣
1:3:6 የማኅበሩ አባላት ሌሎች ጊዜያዊ ችግሮች ሲገጥሙም ሆነ በደስታ ጊዜ ተካፋይ በመሆን ተሳትፎ ያደርጋል፤
1፡3፡7 ለወደፊት ለአባላት ጥቅም ያስገኛል ብሎ የሚያምንበትን ማንኛውንም ዓላማ እንዳስፈላጊነቱ መጨመር
አንቀጽ 1፡4 ትርጓሜ
1፡4፡1 በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴትም ያገለግላል።
1፡4፡2 እድር ማለት የአዲስ እድርና መረዳጃ ማኀበር ማለት ነው።
1፡4፡3 አባል ማለት የአዲስ እድር መተዳደሪያን ደንብ ተቀብሎ የተመዘገበ እና የአባልነት ግዳጁን እየፈጸመ ያለ ግለሰብ ማለት ነው።
1፡4፡4 ቤተሰብ ማለት አባል፣የአባል ባለቤት፣ በእድሩ አባል ስር የሚተዳደርሩ እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማለት ነው።
1፡4፡5 የነርሱና እነርሱ የሚለው እፃጻፍ፤ እርሷ፣እርሱ፣ የእርሱ፣ የእርሷ፣ የእነርሱ፤ የሚሉቱን ቃላቶች ሊተኩ ይችላሉ፡፡
አንቀጽ 1፡5 የእድር ገቢ
1፡5፡1 ከአባልነት ክፍያ፣
1፡5፡2 በስጦታ ከሚገኝ፤
1፡5፡3 እድሩ የሚያዘጋጀውን ፕሮግራም ስፓንሰር ከሚያደርጉ ወይም እርዳታ ከሚሰጡ ድርጅቶች የሚገኝ ገቢ ይሆናል።
ምዕራፍ 2 አባልነት
አንቀጽ 2፡1 አባል ስለመሆን
2፡1፡1 በጆርጂያ ስቴት የሚኖር ዕድሜው 18 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
2፡1፡2 የእድሩን ደንብና ሕግ የተቀበለ ማንኛውም ሰው አባል መሆን ይችላል።
2፡1፡3 አባል ከአካባቢው ለቆ በሌላ ቦታ መኖር ከጀመረ ግዴታውን በማክበር በአባልነት መቀጠል ይችላል።
2,2 የአባልነት ክፍያ አሰባሰብ
2,2.1. የአባልነት ክፍያ በጥሬ ገንዘብ(cash) ማድረግ አይፈቀድም።
2,2,2 የአባልነት ክፍያ እንደ ካሽ አፕ (CashApp) ዜል(Zelle) ሌሎችም ዘመን አመጣሽ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ ፣ በቸክ ወይም በመኒ ኦርደር ብቻ ይደረጋል፡፡ አንቅጽ 2፡2 የአባል መብት፣
2፡2፡1 አንድ አባል ከተመዘገበ ቀን ጀምሮ የመምረጥ መብት አለው።
2፡2፡2 አንድ አባል በአባልነት አንድ ዓመት ከሆነው የመመረጥ መብት ይኖረዋል።
2፡2፡3 አንድ አባል በአባልነት ስድስት ወር ካልሞላው የገንዘብ ጥቅም አያገኝም።
2:2:4 አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከስድስት ወር በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ በአባሉ ወይም በባለቤቱ ወይም በልጁ ላይ የሞት አደጋ ሲገጥም፤ አሥር ሺህ ዶላር ($10,000፡00) ያገኛል።
2.2.4የአባል ልጅ ሐያአንድ ዓመት (21) ሲሞላው፤ምንም ሳይዘገይ ወዲያውኑ የዓመቱን ክፍያ በመክፈል እራሱን ችሎ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ የገባበት ዓመት ከጃንዋሪ አንድ (January 1 st) ጀምሮ እደገባ ይቆጠራል፡፡ እንደሙሉ አባል የተመዘገበበት ዓመት ላይ፡ ከወላጆቹ ጋር ሳለ የሚያገኘውን ጥቅም ያገኛል
2፡2፡5 ከአንድ በላይ በቤተሰብ ላይ ሞት ቢደርስ፣ የእድሩ ቦርድ አባላትንና ማሕበረሰቡን የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርጉ ይጠይቃል፡፡
2፡2፡6፡ ከጆርጅያ እስቴት ውጭ አባል ከሞተ፤ ጉዳዩ እስከሚጣራ፣ እድሩ የተጠቃሚ ገንዘብ ክፍያን ያዘገያል፡፡ የሞት ምስክር ወይም ሌላ ሕጋዊ ወረቀት ማረጋገጫ ለመመልከት እድሩ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
2:2:7 አንድ አባል ከጠፋ ወይም የት እንደደረሰ የማይታወቅ ከሆነ፣ አባሉ የተጠቃሚ ክፍያ አያገኝም ፡፡
2:2:7 ከጥቅም ክፍያ ላይ፡ ያልተከፈሉ ወዝፍ እዳወች አስቀደመው ይቀነሳሉ፡፡
አንቀጽ 2.3 የአባል ግዴታና የባልና ሚስት መብት
2.3.1 የእድሩ ደንብ የሚጠይቀውን መፈጸም፤
2.3.2 የአባልነትና ሌሎች ቅጾችንም በአግባቡ በትክክል ሞልቶ ለእድሩ መስጠት፤
2.3.3 መደበኛ የአባልነት መመዝገቢያና ሌላም በሞት ጊዜ ለሚደረጉ መዋጮዎች በወቅቱ መክፈል፤።
2.3.4 አስገዳጅ ሁኔታ ካላጋጠም በስተቀር በጠቅላላ ስበሰባ ላይ መገኘት፤
2.3.5 በአባላት መካከል የመግባባትና የመተባበር ስሜት አንዲዳብር መርዳት፤
2.3.6 አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ከተለየ እያንዳንዱ የእድሩ አባል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመ በስተቀር፣ለቅሶ መድረስና እዚህ የሚቀበር ከሆነ በቀብሩ ላይ መገኘት፣ አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ወይም ሌላ ቦታ የሚሄድ ከሆነም መሸኘት፤
2.3.7 አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ከተለየ፣ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ አባል ለእድሩ ተጠሪ ማሳወቅ፤
2.3.8 የአባል ወይም የአባል ቤተሰብ ሁኔታ ከተለወጠ፣ (ለምሳሌ የልጅ እድሜ ከ21 በላይ ከሆነ፣ ወይም ባልና ሚስት ከተፋቱ፣) ፣ ለውጥ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውሰጥ ለውጡን ለእድሩ ማሳወቅ ይኖርበታል።
2.3.9 በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ ተጨማሪ አዲስ ልጅ ከተወለደ ወይም ከ21 ዓመት በታች የሆነ የአባል ልጅ ከኢትዮጵያ ወይም ከሌላ ሥፍራ በማምጣት ቤተሰቡን ከተቀላቀለ ለያንዳንዱ ተጨማሪ ልጅ የመመዝገቢያ መቶ ዶላር ($100.00) በመክፈል አባል ይሆናሉ። ማሳሰቢያ፤ ከላይ የተጠቀሰው አባል ከነልጆች የተመዘገበን አይመለከትም
2.3.10 ባልና ሚስት በአንድ ቀን ከተመዘገቡ፤ የአባልነት መብታቸው እኩል ነው፡፡ በምዝገባ ላይ ሁለቱም መገኘት አለባቸው፡፡
2.3.11 አባልና የአባል ባለቤት በተለይየ ጌዜ ከተመዘገቡ፤ የእያንዳዳቸው መበት የሚጀምረው ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
2.3.12 አባልና የአባል ባለቤት በሕጋዊ መንገድ ከተፋቱ፤ አዲስ እድር ማንኛውንም የአባልነት ባለቤትነት ሕጋዊ ውሳኔ ያከብራል፡፡ ሕጋዊ ውሳኔ፣ የባልና የሚስት የግል ስምምንትን በኖተራይዘድ (notarized) ደብዳቤን ያጠቃልላል፡፡ አባል ሁኖ የቀረው፡ የውዝፍ እዳውን ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
2.3.13 የተፈታው አባል የዓመቱን መዋጮ ብቻ በመክፈል እንደአባል ወዲያውኑ (በተፋቱበት ቀን) ሊቀጥል ይችላል። ካልቀጠለ ግን፡ የሞት አደጋ ቢያጋጥም፤ የተጠቃሚ ክፍያውን ያጣል፡፡
አንቀጽ 2፡4 የአባልነት መመዝገቢያና ዓመታዊ ከፍያ
2፡4፡1 የአባነልነት መመዝገቢያ አንድ ጊዜ ብቻ ዓመታዊ
– ግለሰብ $ 250.00 + $240.00
– ቤተሰብ $ 250.00 + $360.00
2፡4፡2 አዲስ አባል የመመዝገቢያ $ __250.00______ እና አመታዊ መዋጮ ግለሰብ ከሆነ 240.00 ቤተሰብ ከሆነ $360.00 አንድ ጊዜ ከፍሎ ይገባል።
2:4.3 በወረረሽኝ በሽታ ወይም በከፍተኛ አደጋ ምክኒያት፡ የተጠቃሚ ክፍያው እድሩ ካለው ገንዘብ በላይ ከሆነ፣ ጠቅላላ ስብሰባ ተጠርቶ፡ ወይም የእድሩ ቦርድ አባላት በወሰኑት የተጠቃሚ ክፍያ ማስተካከል ይደረጋል፡፡
2:4:4 የእድሩ ተቀማጭ ገንዘብ ከመቶ ሽ ዶላር ($50,000) በታች ከሆነ፤ አባላት ተጨማሪ መዋጮ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ፡፡ መዋጮው በአባላቱ በስብሰባ ላይ ይወሰናል፡፡
ምዕ ራ ፍ 3
አንቀጽ 3.1 የሥነ ሥርዓት እርምጃ
3፡1፡1 የአባልነት ክፍያ በዓመቱ መጀመርያ (January) ይጀምራል።
3:1:2 ማንኛውም አባል ወርሀዊ የአባልነት ክፍያውን በዓመቱ መጀመርያ በአንድ ጊዜ ጃንዋሪ ( January) ላይ፤ ወይም በአመት ሁለት ጊዜ ጃንዋሪ(January) እና ጁላይ (July)ላይ እጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤
3:1:2 አንድ አባል ከመክፈያው ጊዜ ሁለት ወር ካሳለፈማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። መክፈል የሚገባውን ክፍያ ሳይከፍል የመክፈያው ጊዜ ሶስት ወር ካለፈ ግን የመቶ ብር ($100) ይቀጣል፡፡ የአባልነት ክፍያውን አንቀፅ
2፡3፡3፡ ይመልከቱ፡፡ 3.1.2 አንድ አባል መክፈል የሚገባውን ክፍያ ሳይከፍል የመክፈያው ዓመት በስድስት (6 month) ወር ካለፈ: በገዛ ፈቃዱ እንደለቀቀ ተቆጥሮ ከአባልነት ይሰናበታል፡፡ የገንዘብ ወይም ሌላ ከእድሩ የሚያገኘው ጥቅሙም ይሰረዛል፡፡
3.1.3 አንድ አባል ለረጅም ጊዜ ከአገር (USA) ውጭ የሚቆይ ከሆነ፡ ቅድመ ክፍያ ለዓመታት ሊያደርግ ይችላል፡፡
3.1.4 የአባልነት ግዴታውን ባለመክፈሉ የተሰናበተ አባል እንደ አዲስ ሊመዘገብ ይችላል። የአባልነት መብቱም እንደ ማንኛውም አዲስ አባል ይሆናል።
3.1.5 አንድ አባል የሐሰት መረጃ ለእድሩ ከሰጠና በዚህም የሃሰት መረጃ ምክንያት ሊሰጠው የማይገባውን ገንዘብም ይሁን ሌላ ጥቅም ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ከተገኘ እና ከተረጋገጠ፣ እድሩ አባልነቱን ሊሰርዝ ይችላል። ያገኘውም ጥቅም ካለ፣ እንዲመልስ እድሩ በህግ ይጠይቀዋል። በዚህ ሁኔታ የተገለለውን አባል፤ እድሩ ሁለተኛ ለአባልነት አይቀበለውም።
3.1.6 አንድ የእድር አባል ከአባልነት ከተገለለ፣ አባል በነበረበት ወቅት ለዕድሩ የከፈለው ማንኛውም ገንዘብ አይመለስለትም።
አንቀጽ 4
የእድሩ የአመራር አካላት
ዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አስፍጻሚ፣ባለ አደራ ቦርድና ኦዲተር ይኖረዋል።
አንቀጽ 4.1
ጠቅላላ ጉባኤ
4.1.1 ጠቅላላ ጉባኤ ማለት የእድሩ አባላት የሚገኙበት ጠቅላላ ስብሰባና የዕድሩ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው።
4.1.2 ጠቅላላ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ ይጠራል። ሁለትኛው ለሽርሽር (picnic) ነው።
4.1.3 ከግማሽ በላይ አባላት የተገኙበት ጠቅላላ ስብሰባ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል።
4.1.4 ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ምልዓተ ጉባኤ ካልሞላ፣ ተከታይ ሁለተኛ ስብሰባ ጠርቶ የሚገኙ አባላት ከግማሽ በታች ቢሆኑም። ስብሰባው እንደምልዓት ጉባኤ እንደሞላ ይቆጠራል።
4.1.5 ከላይ በአነቀጽ 4.1.3 እና 4.1.4 በተጠቀሰው መሰረት ምልዓተ ጉባኤው በታች በአንቀጽ 4.1.6 የተጠቀሰውን ሳያጨምር ሌላ ማንኛውንም ውሳኔ ማስተላለፍ ይችላል።
4.1.6 እድሩን ለማፍረስ የጠቅላላ ጉባኤው ሁለት ሶስተኛው (2/3) ድምጽ ያስፈልጋል።
አንቀጽ 4.2 የጠቅላላ ጉባኤ ተግባርና ሥልጣን
4.2.1 የዳይሬክተሮች ቦርድ ይመርጣል፣
4.2.2 የእድሩን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቃል፣ ያሻሽላል፣
4.2.3 የእድሩን የሥራ ማስኬጃ ወጭ ይፈቅዳል፣
4.2.4 ኦዲተሮችን ይመርጣል፣
4.2.5 የእድሩን ገቢ አሰባሰብ፣ ወጪ አደራረግና ሌሎች የእድሩን የገንዘብ አጠቃቀምና እንቅስቃሴ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
4.2.6 የቦርዱን ሪፖርት ያዳምጣል፣ ይመረምራል፣ እንደአስፈላጊነቱም መመሪያዎችን ይሰጣል::
አንቀጽ 4.3
የዳሬክተሮች ቦርድ የእድሩን ስራ በቅርብ እንዲቆጣጠር በጠቅላላው ጉባኤ የሚሰየም አንድ የዳሬክተሮች ቦርድ ይሰየማል፡፡ ተግባራቱም የሚከተሉት ይሆናል፡፡
4.3.1 የቦርድ አባላት ቁጥር ዘጠኝ ይሆናል፡፡
4.3.2 የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል። ነገር ግን ባልተጠበቀ ምክኒያት የአባላቱ የሥራ ዘመን ለሁለት የሥራ ዘመን ሊራዘም ይችላል፡፡
4.3.3 በሁለት የሥራ ዘመናት በተከታታይ ያገለገለ የቦርድ አባል በድጋሚ ለመመረጥ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በቦርድ አማካሪነት ማገልገል ይኖርበታል። በቦርድ ስብሰባ ውሳኔ ላይ አይመርጥም፡፡
4.3.4 የቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይሆናል።
4.3.5 በማናቸውም የቦርድ ምርጫ ጊዜ ከአባላቱ ከሚቀርቡት ውስጥ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱ የቦርድ አባላት ቁጥር ከ50 በመቶ ወይም ከግማሽ ሊበልጥ አይችልም።
4.3.6 አንድ የቦርዱ አባል የሥራ ዘመኑን ሳይጨርስ አገልግሎቱን በማናቸውም ምክንያት ቢያቋርጥ ለቀሪው የሥራ ዘመን ተክቶ የሚያገለግል አባል ቦርዱ ከአባላት መሃል ይሰይማል።
4.3.7 በማናቸውም የቦርድ አባላት ምርጫ ጊዜ የቦርዱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆነ አባል ተመልሶ ለቦርድ አባልነት ቢመረጥ ቀድሞ ይዞት የነበረውን የስራ አስፈጻሚ ስፍራ መልሶ ሊይዝ አይችልም።
አንቀጽ 4.4
የዳይሬክተሮች ቦርድ ተግባርና ስልጣን የሚከተሉት ይሆናል።
4.4.1 ከቦርዱ አባላት መካከል ቦርዱ ሰባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል።
4.4.2 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የእድሩን ስራ ለማካሄድ የሚያወጣቸው የአፈጻጸም ስርዓቶችን ይመረምራል፣ ያጸድቃልም።
4.4.3 የሥራ አፈጻጸም ዘገባ ለጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።
4.4.4 የእድሩ ወጪ በጠቅላላ ጉባኤ ከተፈቀደው በላይ አለመሆኑን ይቆጣጠራል፣ ወጪው ከተፈቀደው መጠን ከአስር በመቶ (10%) በላይ ከሆነ ይህ የሆነበትን ምክንያት ለጠቅላል ጉባኤው ያስረዳል።
4.4.5 ማንኛውም የቦርዱ አባል ለእድሩ ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ወይም መደጎሚያ አይደረግለትም።
4.4.6 እንደ አስፈላጊነቱ የእድሩ ሊቀመንበር በእድር ጉዳይ ላይ ልምድ ወይም እውቀት ያላቸውን የእድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያውያንን ወይም ከሌላ አገር ይጋብዛል።
ሆኖም ግን እነዚህ አማካሪዎች ልምዳቸውን ከማካፈልና ሃሳብ ከመስጠት ውጭ በቦርድ ስብሰባ ላይ ድምጽ አይሰጡም።
4.4.7 የቦርድ ምርጫ በሁለተኛው ዓመት በሚደረግ ስብሰባ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 4.5 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ኃላፊነት
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፣አንድ ሊቀመንበር፣ አንድ ምክትል ሊቀመንበር፣ አንድ ፀሃፊ፣ አንድ አቃቤ ንዋይ ( ገንዘብ ያዥ)፣
እንድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ አንድ የኦፕሬሽንና የቴክኖሎጂ ኃላፊና፣ አንድ የሂሳብ ባለሙያ (አካውንታንት) ያሉበት ባለ ሰባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡ ይህ ኮሚቴም የሚከተሉት ተግባራት ያከናውናል።
4.5.1 የእድሩን የእለተ ከእለት ተግባር የሚያከናውን አንድ ሊቀመንበር፣ አንድ ምክትል ሊቀመንበር፣ አንድ ፀሃፊ፣ አንድ አቃቤ ንዋይ (ገንዘብ ያዥ)፣ይመርጣል፡፡
4.5.2 ለሥራው ክንውን የሚረዱ የስራ አፈጻጸም ስርዓቶች ያሰናዳል። በቦርድ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ያውላል።
4.5.3 የዕድሩን ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣ መመሪያ ያወጣል፣ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
4.5.4 እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው እየተገናኘ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
4.5.5 ለቦርዱ የሥራ ክንውን ዘገባ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።
4.5.6 የእድሩን ገቢ ያሰባስባል።
4.5.7 ቅጾችን አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ያውላል።
4.5.8 በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እርዳታ ይሰጣል።
4.5.9 አስፈላጊ ኢንፎርሜሽን ለአባላት በወቅቱ አንዲደርስ ያደርጋል።
4.5.10 የእድሩን ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ይይዛል።
4.5.11 የእድሩ አሠራር የሚሻሻልበት መንገድ እያጠና በቦርድ ሲፈቀድ ስራ ላይ ያውላል።
አንቀጽ 4.6
ሊቀመንበር
4.6.1 የቦርዱን የሥራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ ስብሰባ በሊቀ-መንበርነት ይመራል።
4.6.2 የእድሩ ስራ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት አንዲከናወን ያቅዳል፣ የእድሩን ስራ ይመራል፣ አባላትን ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል።
4.6.3 የእድሩ ሥራን ይመራል ፡፡ በየጊዜው ለሚደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባን ያስተባብራል፡፡
4.6.4 የሥራ ክንውን ዘገባ በየጌዜው ለሚሰበሰበው ለዳይሬክተሮች ቦርድ ያቀርባል።
4.6.5 የዳይሬክተሮች ቦርድን ስብሰባ ይጠራል፡፡ አስቸኳይ ሁናቴ ካጋጠመው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሃሳብ ያቀርባል።
4.6.6 የወጭ ማዘዣዎችንና ደብዳቤዎችን በዕድሩ ስም ይፈርማል።
እንቀጽ 4.7 ምክትል ሊቀመንበር
4.7.1 ሊቀመንበሩ በማይገኝበት ጊዜ ሊቀመንበሩን ተክቶ የእድሩን ሥራ ያከናውናል።
አነቀጽ 4.8 ጸሐፊ
4.8.1 የዕድሩን አባላት የስም ዝርዝር ይይዛል።
4.8.2 የቦርዱንና የስራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ አጀንዳ አዘጋጅቶ ሊቀመንበሩ ሲፈቅድ በየወሩ የስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አባሎችን፣ በየሶስት ወሩ የባለአደራ ቦርድ እባላትን
እንዲሁም በየጊዜው ሲወሰን የእድሩን ሙሉ አባላት ለስብሰባ ይጠራል።
4.8.3 የስብሰባዎችን ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ያዘጋጃል፣ ለቦርዱ ያቀርባል።
4.8.4 የእድሩን ጽህፈት ቤት ሥራ ያከናውናል።
አንቀጽ 4.9 ገንዘብ ያዥ
4.9.1 በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለእድሩ ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብ በየጊዜው እየሰበሰበ በእድሩ የባንክ ሂሳብ ያስቀምጣል።
4.9.2 በመመሪያው መሰረት ዕድሩ ለአባሎች የሚሰጠውን ዕርዳታ ወይም ክፍያ ቦርዱ ሲወስን ይፈጽማል።
4.9.3 ቼኮች በሁለት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎች መፈረማቸውን ያረጋግጣል፡፡
4.9.4 የእድሩን ሥራ ማካሄጃ በጀት ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ያውላል።
4.9.5 ወጪዎቹ በበጀት ከተፈቀደው በላይ አለመሆናቸውን ይከታተላል።
አንቀጽ 4.10 የሂሳብ ሹም (አካውንታንት)
4.10.1 የእድሩን የሂሳብ መዛግብት ይይዛል።
4.10.2 የእድሩን የገቢና የወጪ ደረሰኞች ይይዛል።
4.10.3 ገቢዎች በአግባቡ የተሰበሰቡ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል። 4.10.4 የባንክ ደብተሮች ይይዛል፣ ያስታርቃል። 4.10.5 የእድሩን ሂሳብ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ያቀርባል። 4.10.6 በመንግስት ተቋማት የሚጠየቅ የሂሳብና የታክስ ሪፖርት ያዘጋጃል።
አንቀጽ 4.11 የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
4.11.1 በማንኛውም እድሩን በሚመለከት ሁኔታ የሚደረገውን የማሰተዋወቅ ሥራ ያከናውናል።
4.11.2 ከተለያዩ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይመሰርታል።
4.11.3 እድሩን ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ ጽሁፎችን አያዘጋጀ በየቦታው ይበትናል።
4.11.4 ማንኛውንም የዕድሩን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ለአባላት ያስተላልፋል ወይም መተላለፍን ያረጋግጣል።
4.11.5 የእድሩን ዓላማ ሊያግዝ ከሚችሉ ተቋማት ሊገኝ የሚችለውን ጥቅምና እርዳታ እየተከታተል ለቦርዱ ያቀርባል።
4.11.6 የእድሩን ዓላማ ለማስፈጸም ከሚያግዙ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመስረት ስለዝርዝር ሥራቸው ለቦርዱ ሪፖርት በማቅረብ ዕድሩ በተሻለ ሁኔታ አገልግሎች የሚያገኝበትን መንገድ ያበጃል።
አንቀጽ 4.12 የኦፕሬሽንና ቴክኖሎጂ ኃላፊ
4.12.1 የእድሩ አሠራር በሚቀላጠፍበት ሁኔታ ላይ አጠቃላይ ጥናቶችን እያደረገ ሪፖርቱ ያቀርባል።
4.12.2 ስለ ቀብር ቤቶች፣ትራንስፖርት፣ ፓሊስ፣ እና ሰለመሳሰሉት ከዕድሩ ሥራ ጋር ሰለሚገናኙ ተቋማትና አገልግሎቶች አስፈላጊውን ጥናት እና ክንውን ሪፖርት ለቦርዱ ያቀርባል።
4.12.3 ዕድሩ ከጋራ ዋስትና ወይም መድሕን ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ አጥንቶ ለቦርዱ ሪፖርት ያቀርባል።
4.12.4 የእድሩን ዓላማ ለማስፈጸም ያግዛሉ ተብለው የሚገመቱ ኮሚቴዎችን የማቋቋም ጥረቱን በኃላፊነት ይመራል።
4.12.5 ዕድሩ ሕጋዊ አካል ለማግኘትና ይህን ይዞ ለመቆየት የሚያስፈልገውን ሁኔታ በመከታተል ስራ ላይ ያውላል።
4.12.6 የእድሩን ድህረ-ገጽ የማቋቋሙን፣ የማስተደደሩንና የማሳደጉን ጥረት በኃላፊነት ይመራል።
4.12.7 የዕድሩን የዶመይን (ድህረ ገጽ) ስም ያስመዘግባል፣ ምዝገባውም አንዳያልፍበት በየዓመቱ አስፈላጊውን ዕድሳት ያደርጋል።
4.12.8 አባላት የዕድሩን ድህረ ገጽ በሚገባ የሚጠቀሙበትን ሁኔታ እያጠና ለቦሩድ በማቅረብ ጥናቶችን ስራ ላይ ያውላል።
አንቀጽ 4.13 ኦዲተር
4.13.1 የዳሬይክተሮች ቦርድ ከጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ ሶስት አባላት ያሉበት ኦዲተሮችን ይሰይማል። 4.13.2 የኦዲተሮቹም ተጠሪነት ለቦርዱ ይሆናል። 4.13.3 ኦዲተሮቹም በሂሳብ ባለሙያው ተዘጋጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፓርት መርምረው የደረሱበትን ለቦርዱ ያቀርባሉ። 4.13.4 ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ኦዲተሮቹ ሙሉውን ዓመት የሚያጠቃልል፣ የወራት፣ የሩብ ዓመት፣ ወይም የግማሽ ዓመታት ሪፖርቶችን እንዲያቀርቡ ሊጠይቅ ይችላል።
ምእራፍ 5 ባለ-አደራ ቦርድ አንቀጽ
5.1 አመሠራረትና ኃላፊነት
5.1.1 አምስት (5) አባላት ያሉበት ባለ-አደራ ቦርድ ከጠቅላላው ጉባኤ አባላት ይሰየማሉ።
5.1.2 የእድሩ ምክትል ሊቀመንበርና የሂሳብ ሹም ምንጊዜም የባለ-አደራ ቦርድ አባል ይሆናሉ፡፡ የእድሩ አባላትሶስት (3) ሌላ ሰወች ይመርጣሉ፡፡
5.1.3 ከተመረጡት አንዱ የባለ-አደራ ቦረድ ሰብሳቢ ይሆናል፡፡
5.1.4 የባለ-አደራ ቦርድ በቀጥታ ተጠያቂነቱ ለኢትዮ እድር ጠቅላላ ጉባዔ ይሆናል።
5.1.5 ለባለ-አደራ ቦርድ ከተመረጡት አንዱ ሥራዉን በሆነ ምክኒያት ሊቀጥል ባይችል፤ ሐላፊነቱን ቢያስረክብ፤ ወዲይውኑየማሕበሩ ዋና ቦርድ ሌላ ይተካል ለአባላትም ያስታውቃል።
5.1.6 የባለ-አደራ ቦርድ ከአዲስ እድር ዳሪክተሮች ቦርድ ጋርና፣ ከሌላው አባል ጋር በመነጋገርና በመመካከር፤ አዲስ እድር ላለው ገንዘብና ንብረት ጥበቃና ደህንነት ተባብሮ ይሠራል
ይቆጣጠራልም።
5.1.7 ከአሥር ሺ ዶላር ($10,000.00) በላይ ወጭ ሲሆን (ከተጠቃሚ ክፍያ ሌላ) ፤ የባለ አደራ ቦርድ ማጽድቁን በጹሑፍ ይገልጣል።
5.1.8 የባለ-አደራ ቦርድ ጎድሎ አሠራርን ከተገነዘበ፤ መጀመሪይ ጉዳዩን ወደ እድር ቦርድ ይቀረባል፡፡ አጥጋቢ ውጤት ካላገኘ፤ ጉዳዩን ወደ ኢትዮ እድር ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል፡፡
አሰቸኻይ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡
5.1.9 የአባላትን እሮሮ በቦርድ ላይ ያለዉን ይቀበላል።
5.1.10 ቢቻል በየወሩ ካልተቻለ በየሶስት ወሩ፣ ክባንክ ያለውን ገንዘብ እንዲሁም የእድሩን ንብረት ያገናዝባሉ፡፡
አንቀጽ 5.2 የባለ-አደራ ቦርድ ምርጫና የሥራ ዘመን
5.2.1 ለባለ-አደራ ቦርድ አባልነት የሚመረጡ ት ሶስቱ (5) እጩዎች ለሶስት (3) አመታት ያገለግላሉ።
5.2.2 ከአባል በሥራ ስንብት ምክንያት ክፍት ቦታ ቢኖር፣የኢትዮ እድር ቦርድ እስከቀጣዩ ጠቀላላ ስብሰባ ድረስ ተተኪ ባለአደራ አባላን መሰየም ይቻላል።
5.2.3 የባለአደራ ቦርድ አባላት፣ የሥራ ዘመናቸው ሲያበቃ፣ በድጋሚ ተመርጠው ለማገልገል የሚያግዳቸው አይኖርም።
ምእራፍ 6 የእድሩ ሕገ-ደንብ (Bylaw)
6፡1 ይህ ሕገ-ደንብ በ2023 የተዘጋጀ የአዲስ እድርና መረዳጃ ማኀበር ሕገ-ደንብ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። ከ ______ከጃንዋሪ (January 23023)___ ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል።
6.2 የአዲስ እድር አመታዊ የስራ አፈፃፀም እና የሒሳብ አያያዝ በ January 1st የሚጀምር ሲሆን የዓመቱ ሒሳብ በDecember 31st ይዘጋል። (Annual cycle will be January 1st to December 31st).